የሥልጠና፣ የቤት ለቤት ዝግጅት ወይም የማኅበረሰብ ክሊኒክ ጥያቄ

የሥልጠና፣ የቤት ለቤት ዝግጅት ወይም የማኅበረሰብ ክሊኒክ ጥያቄ

ትምህርት ቤቶች፣ ቤተሰቦች፣ እና ማኅበረሰቦች ተማሪዎችን የሚደግፉ፣ የቤተሰብ-ትምህርት ቤት ግንኙነትን የሚያሻሽሉ እና የትምህርት ዕድል ክፍተትን የሚቀንሱ ውሳኔዎችን ለመወሰን ከአንድ ተመሳሳይ ቦታ ላይ መጀመር እንዲችሉ የእኛ የሕዝብ K-12 ትምህርት ቤቶች እንዴት እንደሚሠሩ ቤተሰቦች እና ማኅበረሰቦች ያላቸውን ግንዛቤ እናሻሽላለን።

ነጻ የትምህርት ዝግጅቶችን፣ ሥልጠናዎችን እና የቤት ለቤት ግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራዎችን በመጠነ ሰፊ ጉዳዮች ዙሪያ እናቀርባለን።  በተጨማሪ የእኛን የእንባ ጥበቃ አገልግሎቶች በቀጥታ ወደ የእርስዎ ሰፈር በቻልንበት ጊዜ ለማምጣት ከመንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ወይም ትምህርት ቤቶች ጋር በአጋርነት በመሥራት የማኅበረሰብ ክሊኒክ አገልግሎቶችን እናቀርባለን።

በቅርቡ የሰጠናቸው ሥልጠናዎች ግጭት አፈታትን፣ የቤተሰብ ተሳትፎን፣ ትንኮሳን፣ ማስፈራራትን እና በጉልበት ማሰቃየት (HIB)፣ የትምህርት ቤት ዲስፕሊንን፣ ቤት ለሌላቸው ወይም በማደጎ ላሉ ወጣቶች ድጋፍ፣ የቋንቋ መዳረሻ፣ እና የአካል ጉዳት ላለባቸው ተማሪዎች የሚሰጡ አገልግሎቶችን የሸፈኑ ነበሩ። ያለን ውስን የሠራተኛ ብዛት ተጠቅመን የማኅበረሰብ አቅምን በመገንባት ያለንን ተደራሽነት ለማስፋት ከፍተኛ ፍላጎት አለን።  ጥሩ መረጃ ካልዎት፣ በርካታ ተማሪዎች ስኬታማ እንዲሆኑ ማገዝ ይችላሉ!

OEO ለቤተሰቦች፣ የማኅበረሰብ ቡድኖች እና መሪዎች እና መምህራን ፍላጎታቸውን ለማሟላት ሲባል ሥልጠናዎችን እንደ አስፈላጊነቱ ማስተካከል ይችላል።  ስለ የእኛ አገልግሎቶች በትንሹ ግንዛቤ እንዲኖርዎት ለማስቻል ከዚህ በታች ጥቂት የ OEO ሥልጠናዎች ናሙና ቢጋሮች ተዘርዝረዋል፦

ከ የእኛ ስትራቴጂያዊ ዕቅድ ሥር፣ የሚከተሉት ሁኔታዎች ላይ ያሉ K-12 ተማሪዎችን ችግሮች መፍትሔ የሚሰጡ ሥልጠናዎችን እና ዝግጅቶችን እስከ 2023 በማስፋፋት ላይ እንገኛለን፦

 • በከፊል የትምህርት ቀናትን አክብረው እንዲገኙ የተፈቀደላቸው የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎችን ጨምሮ ከትምህርት ቤት ውጭ ያሉ ተማሪዎች
 • ነጭ ያልሆኑ ሰዎች፣ ጥቁሮች ወይም ቀይ ህንዶች 
 • የመኖሪያ ቤት እጦት ችግር ላይ ያሉ
 • በዘመድ ወይም በማደጎ እንክብካቤ ሥር ያሉ 
 • በወጣት አጥፊ ማረሚያ ወይም በወጣት አጥፊ መልሶ ማቋቋሚያ ሥርዓቶች ውስጥ ያሉ
 • ስደተኛ፣ ፍልሰተኛ፣ ጥገኛ፣ ወይም ማይግራንት፣ ወይም የመጀመሪያ ቋንቋ(ቸው) እንግሊዝኛ ያልሆኑ ተማሪዎች ወይም ቤተሰቦች፣ ወይም
 • Wraparound with Intensive Services (WISe፣ ራፕአራውንድ ከልዩ አገልግሎቶች ጋር) ወይም Children’s Long Term Inpatient Programs (CLIP፣ የልጆች የረዥም ጊዜ ታካሚዎች ፕሮግራም) ድጋፍ የሚያገኙ

OEO ለጉዞ እና የሚከተሉት ላይ የሚደርሱ ዝግጅቶችን በአማራጭነት ለማቅረብ ያሉት ሠራተኞች ብዛት ውስን ነው፦

 • በርከት ያሉ ታዳሚዎች
 • በእኛ ስትራቴጂያዊ ዕቅድ ውስጥ ሊገቡ የሚችሉ እና የትምህርት ርትዓዊነትን ሊጨምሩ የሚችሉ አሳሳቢ ነገሮች
 • አሠልጣኞችን ማሠልጠን ሞዴል በመጠቀም የማኅበረሰብ አቅምን መገንባት
 • እንደ መስተጋብራዊ በበይነመረብ በቀጥታ የሚሰጡ ትምህርቶችን የመሳሰሉ በበይነመረብ ሊሰጡ የሚችሉ ትምህርታዊ ዝግጅቶች

የእኛ ቡድን የአካል ጉዳተኞች ፍትሐዊ አያያዝ እንዲያገኙ እና የአካል ጉዳተኛ እና የቋንቋ ተደራሽነት መኖሩን ለማረጋገጥ ቁርጠኛ አቋም አለው

በእርስዎ ቀጣይ ዝግጅት ላይ የእኛ ቡድን እንዲገኝ የሚፈልጉ ከሆነ፣ ይህን የእኛን ሁሉን አሳታፊ ለመሆን የምናደርገውን ጥረት ለመደገፍ የሚከተሉትን እርምጃዎች እንዲወስዱ እንጠይቅዎታለን፦

 • ለቋንቋ እና አካል ጉዳት ተደራሽነት እና መስተንግዶ ከተጠሪው ሰው ጋር በመሆን ተደራሽ የሆኑ በራሪ ወረቀቶችንውወይም ሌሎች የዝግጅት ማስተዋወቂያ ማቴሪያሎችን ማዘጋጀት
 • እነዚህን መስተንግዶዎችን እና መዳረሻዎችን ለማቅረብ ቁርጠኛ አቋም መያዝ
 • ዝግጅቱን በአካል ሊደረስበት በሚችል ቦታ ላይ ማዘጋጀት
 • ለተሳታፊዎች ድምፅ ማጉያዎችን ማቅረብ (ለምሳሌ ማይክራፎን፣ ስፒከሮች)

በምላሹ፣ እንደ የእርስዎ አጋር የሚከተሉትን እናደርጋለን፦

 • የእኛ ትምህርታዊ ዝግጅት ማቴሪያሎች እና እንቅስቃሴዎች ተደራሽ መሆናቸውን ማረጋገጥ
 • ስለ መዳረሻ እና ግብዓቶችን ለይቶ ይበልጥ ማወቅ መቻል ላይ እርስዎን ማገዝ

ከእርስዎ ጋር ለመተባበር እንፈልጋለን!

የእርስዎን ተደራሽነት ጉዞ መጀመር የሚችሉበት አንድ ቦታ ቢኖር የእኛ Guide to Accessible Event Planning ነው። መዳረሻን ስለማሻሻል ዝርዝር መረጃዎችን እዚህ ላይ ማግኘት ይችላሉ።

የትምህርት ዝግጅትን፣ ሥልጠናን፣ የቤት ለቤት ዝግጅትን ወይም ክሊኒክ ለማዘጋጀት ፍላጎቱ ያልዎት ከሆነ፣ ስለ ተገኝነት ጥያቄ ለመጠየቅ እባክዎ oeoinfo@gov.wa.gov ን ያነጋግሩ።