በዋሽንግተን ግዛት ውስጥ የሚኖሩ ሁሉም ልጆች የህዝብ ትምህርት የማግኘት መብት አላቸው።
ልጆች መዋእለ ህጻናትን ከ 5 አመታቸው መጀመር እና እስከሚመረቁ ወይም 21 አመት እስኪሞላቸው በትምህርት መቀጠል ይችላሉ።
በመመዝገብ (ወይም በምዝገባ) ይጀምራል። ስለ ትምህርት ቤቱ ምዝገባ የምናገኛቸው ጥያቄዎች የሚያካትቱት፦
- ለምዝገባ ምን አይነት መረጃ ወይም የተጻፈ ወረቀት ያስፈልጋል?
- ተማሪውን ማስመዝገብ የሚችለው ማን ነው?
- ተማሪው የት መመዝገብ ይችላል፣ ወይም ወላጅ የቱን ትምህርት ቤት መምረጥ ይችላል?
ከታች ያሉትን ጥያቄዎች ይጫኑ።
- በአጠቃላይ ለምዝገባ ምን አይነት መረጃ ወይም የተጻፈ ወረቀት ያስፈልጋል?
-
አንድን ተማሪ በትምህርት ቤት ለመመዝገብ፣ በአጠቃላይ ትምህርት ቤቶች የሚከተሉትን ሰነዶች ይጠይቃሉ፦
አድራሻዎትን ያረጋግጡ፤ የልጅዎን እድሜ (በተለይ ለመዋእለ ህጻናት ምዝገባ)፤ እና ልጅዎ የሚያስፈልገውን ክትባት ማግኘቱን ያሳዩ።ትምህርት ቤቱን ወይም የትምህርት ቤቱን ዲስትሪክት ቢሮ ለእርዳታ መጠየቅ ይችላሉ። እንዲሁም በ 1-866-297-2597 በመደወል ቢሯችንን ማነጋገር ይችላሉ ወይም በኦንላይን የመቀበያ ስርዓታችን፦ https://services.oeo.wa.gov/oeo በኩል እገዛችንን ያግኙ የሚለውን ገፅ ይጎብኙ።
በአብዛኛው ትምህርት ቤቶች ለምዝገባ ሊጠቀሟቸው የሚችሉትን ሰነዶች ምሳሌዎችን ይዘረዝራሉ። ትምህርት ቤቱ የሚፈልጋቸውን ልዩ ሰነዶች (እንደ ደረሰኝ፣ ወይም የልጅዎ የልደት የምስክር ወረቀት) ከሌልዎት፣ የትምህርት ቤቱን የምዝገባ ቢሮ ማነጋገር ይችላሉ።
የልደት የምስክር ወረቀት አማራጮች/ፓስፖርቶች፦ ትምህርት ቤቶች የልጁን እድሜ የሚያሳዩ አማራጮችን የመቀበል ግዴታ አለባቸው። የልደት የምስክር ወረቀት ወይም ፓስፖርት ከሌልዎት ትምህርት ቤቱ ለመቀበል አያስገድዶትም። ሌሎች አማራጮች የጉዲፈቻ መረጃ፣ በሃኪም የተረጋገጠ መግለጫ፣ ወይም የልደት ቀን ያለበት የክትባት መረጃን ሊያካትት ይችላል።
የነዋሪነት ማረጋገጫ፦ ትምህርት ቤቶች በአጠቃላይ ልጅዎ የዲስትሪክቱ ነዋሪ መሆኑን ለማረጋገጥ የት እንደሚኖሩ ማስረጃ ይጠይቃሉ። ነገር ግን፣ በአሁኑ ሰዓት ለመኖር መደበኛ መኖሪያ ቤት ከሌልዎት (በመኖሪያ ቤት እጦት እያሳለፉ ከሆነ)፣ ትምህርት ቤቱ ልጅዎን ከማስመዝገብዎ በፊት መረጃ መጠየቅ አይችልም። ይህ ለእርስዎ ወይም እርስዎ ለሚንከባከቡት ልጅ ተፈጻሚ ከሆነ፣ ከትምህርት ቤቱ ዲስትሪክት “McKinney Vento Liaison (ማኪኒ ቬንቶ ህብረት)” ለመነጋገር ትምህርት ቤቱን ወይም የዲስትሪክቱን ቢሮ ይጠይቁ።
ያስታውሱ፣ በዋሽንግተን ግዛት የሚኖሩ ሁሉም ልጆች የህዝብ ትምህርት የማግኘት መብት አላቸው። ልጅዎን ትምህርት ቤት ለማስመዝገብ እየሞከሩ ከሆነ፣ ነገር ግን ትምህርት ቤቱ በአብዛኛው የሚጠይቀው የተጻፈ ወረቀት ከሌልዎት፣ እባክዎን እርዳታ ይጠይቁ።
- ተማሪውን ማስመዝገብ የሚችለው ማን ነው?
-
በዋሽንግተን መንግስት፣ ልጅን ትምህርት ቤት ለማስመዝገብ የሚችሉ ውስጥ የሚካተቱት፦
ወላጆች ወይም ህጋዊ ሞግዚቶችወላጅ ወይም ሞግዚት በማይኖርበት ጊዜ እንደ ወላጅ የሚሰራ ሰው። ይሄ ሊያካትት የሚችለው፦
“ቤተሰባዊ እንክብካቤ” የሚያቀርብ ዘመድ፣ አሳዳጊ ወላጅ፣ ወይም እንደ ወላጅ የመንከባከብ ሚና የሚሰራ።
ታዳጊዎች በራሳቸው። ከወላጅ ጋር የማይኖር፣ እና ቋሚ ወይም በቂ የመኖሪያ ስፍራ የሌለው ታዳጊ፣እንደ “ብቸኛ ቤት አልባ ታዳጊ” በራሳቸው ለመመዝገብ እርዳታ ማግኘት ይችላሉ። በራስዎ የሚኖሩ ወይም ትምህርት ቤት ውስጥ በራሱ የሚመዘገብ ታዳጊ እየረዱ ከሆነ፣ ከ McKinney Vento Liaison ጋር ለመነጋገር ይጠይቁ።
በ Family Educational Rights and Privacy Act (FERPA፣ የቤተሰብ ትምህርታዊ መብቶች እና ግላዊነት አዋጅ) መሰረት፣ የፌደራል ህግ በትምህርት መዝገቦች ላይ፣ "ወላጅ" ”የተፈጥሮ ወላጅን፣ ሞግዚትን፣ ወላጅ ወይም ሞግዚት በማይኖሩበት ጊዜ እንደ ወላጅ የሚሆን ግለሰብን ያካትታል።" (በ U.S. Department of Education (በአሜሪካ የትምህርት ክፍል) ድህረ ገጽ፦ https://www2.ed.gov/policy/gen/guid/fpco/ferpa/index.html ላይ ስለ FERPA ተጨማሪ ማንበብ ይችላሉ።
ልጆች በማደጎ ውስጥ ሲሆኑ፣ ስለ ትምህርታቸው ለመወሰን በመርዳት ላይ ብዙ ሰዎች ሊሳተፉ ይችላሉ። የተንከባካቢ ፈቃድ ቅፅ ብዙ ጊዜ ልጁን በትምህርት ቤት ማስመዝገብን ጨምሮ በትምህርቱ መወሰን የሚችለውን ሰው ይለያል። ለተጨማሪ መረጃ Guide to Supporting Students in Foster Care (ማደጎ ያሉ ተማሪዎችን ለመርዳት የሚያግዝ መመሪያ)፣ ከ Treehouse for Kids (www.treehouseforkids.org)፣ ከ Office of Superintendent of Public Instruction (OSPI፣ የህብረተሰብ መመሪያ ተቆጣጣሪ ቢሮ) Foster Care Program (የማደጎ ፕሮግራም) (https://www.k12.wa.us/student-success/access-opportunity-education/foster-care)፣ እና በቀጥታ እዚህ ሊንክ፦ https://www.treehouseforkids.org/wp-content/uploads/2018/01/treehouse2017final2ndedinteractive.pdf ላይ ይመልከቱ።
- ተማሪው ትምህርት ቤት ውስጥ የት ሊመዘገብ ይችላል?
-
የነዋሪ ትምህርት ቤት ዲስትሪክት
ተማሪው በአብዛኛው ከሚኖርበት ዲስትሪክት ሁሉም ተማሪዎች ከዲስትሪክቱ የትምህርት እድል የማግኘት መብት አላቸው። ይህ የተማሪው “የነዋሪ ትምህርት ቤት ዲስትሪክት” ነው።
የተማሪው መኖሪያ ቢት ከወላጁ መኖሪያ ቤት ጋር አንድ ላይሆን ይችላል።
የዋሽንግተን ግዛት ህግ የተማሪውን መኖሪያ የሚወስነው በ Washington Administrative Code (የዋሽንግተን የአስተዳደር ኮድ)፣ "WAC" በ WAC 392-137-115 ላይ ነው፣ ይህም በኦንላይን በ፦ https://apps.leg. wa.gov/WAC/default.aspx?cite=392-137-115 ላይ ሊያገኙ ይችላሉ። የተማሪው መኖሪያ ቤት ተማሪው ብዙ ጊዜ የሚቆይበት መሆኑን ያብራራል።
በዲስትሪክቱ ውስጥ ያሉ የትምህርት ቤት ምደባዎች
በአጠቃላይ፣ እያንዳንዱ የትምህርት ቤት ዲስትሪክት ተማሪዎችን በዲስትሪክቱ ውስጥ ለሚገኙ ለተለያዩ ትምህርት ቤቶች እንዴት እንደሚመደብ መወሰን ይችላል።
አብዛኛዎቹ የትምህርት ቤት ዲስትሪክቶች ተማሪዎችን በሚኖሩበት አቅራቢያ ወደሚገኝ ትምህርት ቤት ይመድባሉ፣ ብዙ ጊዜ “የክትትል አካባቢ” ወይም የአጎራባች ትምህርት ቤት ይባላል። የአጎራባች ትምህርት ቤቶች በጣም ከሞሉ፣ የትምህርት ቤት ዲስትሪክቶች ተማሪዎችን በዲስትሪክቱ ውስጥ ወዳሉት ሌሎች ትምህርት ቤቶች ሊመደቧቸው ይችላሉ።
ብዙ ትላልቅ የትምህርት ቤት ዲስትሪክቶች ቤተሰቦች በመረጡት ትምህርት ቤት ማመልከት የሚችሉበት "ክፍት የምዝገባ" ጊዜ አላቸው። አብዛኛውን ጊዜ ከአመቱ መጀመሪያ አቅራቢያ ጀምሮ እስከ ጸደይ መጀመሪያ ድረስ ነው። ስለ ትምህርት ቤት ምዝገባ አማራጮች ከዲስትሪክትዎ የሚሰጠውን መረጃ ይመልክቱ።
ተማሪው አንዴ በአንድ ትምህርት ቤት ከተመደበ በኋላ፣ አንዳንድ ዲስትሪክቶች ወደ ሌላ ትምህርት ቤት ለመዛወር የሚፈቅዱት በችግር ወይም ተመሳሳይ ምክንያት ካለ ብቻ ነው። ሌሎች ክፍት ቦታ ካለ ዝውውር ይፈቅዳሉ። በዲስትሪክትዎ ውስጥ ስላሉ አማራጮች የበለጠ ለማወቅ የዲስትሪክትዎን ፖሊሲዎች እና ሂደቶችን ይጠይቁ።
ያስታውሱ፣ እያንዳንዱ ልጅ ከሚኖርበት የትምህርት ቤት ዲስትሪክት ትምህርት የማግኘት መብት አለው። ከመመዝገብ የሚያግድዎት ነገር ካለ፣ መስሪያ ቤታችንን በ 1-866-297-2597፣ oeoinfo@gov.wa.gov ላይ ኢሜይል በመላክ ወይም በኦንላይን መቀበያ ሲስተም፦ https://services.oeo.wa.gov/oeo በኩል ማነጋገር ይችላሉ።
የመጀመሪያ ትምህርት ቤት - ማደጎ ወይም ቤት እጦት ማጋጠም
ቤት እጦት ያጋጠማቸው ልጆች እና በማደጎ ውስጥ ያሉ ልጆች አሁን በሚቆዩበት አካባቢ ትምህርታቸውን መከታተል ይችላሉ ወይም ወደ ሌላ አካባቢ ቢዘዋወሩ እንኳን “በመጀመሪያው ትምህርት ቤት” እንዲቆዩ እርዳታ ማግኘት ይችላሉ።
የቤት እጦት ለሚያጋጥማቸው ተማሪዎች ጥበቃ እና ድጋፍ የሚሰጠው የ“McKinney Vento Act”(የማክኒ ቬንቶ አዋጅ) ይባላል፣ እና እያንዳንዱ የትምህርት ቤት ዲስትሪክት የቤት እጦት ያለባቸውን ቤተሰቦች እና ተማሪዎች ለመርዳት የ McKinney Vento Liaison እርዳታ አለው። ይህም የራሳቸው ቦታ ስለሌላቸው ከጓደኞቻቸው ወይም ከዘመዶቻቸው ጋር አብረው ያሉትን ተማሪዎች እና ቤተሰቦች ሊያካትት ይችላል። እርስዎ ወይም ልጅዎ በመነሻ ትምህርት ቤት ውስጥ መቆየትን ጨምሮ ለ McKinney Vento (ማክኒ ቬንቶ) ድጋፎች ብቁ የሚሆኑበት እድል ካለ፣ እባክዎ የትምህርት ቤቱን ዲስትሪክት “McKinney Vento Liaison” ለማነጋገር ይጠይቁ። እንዲሁም የቤት እጦት ስላጋጠማቸው ተማሪዎች የሚደረጉ ድጋፎችን በተመለክተ በድረ-ገጻችን ላይ ተጨማሪ መረጃ መመልከት ይችላሉ።
“ESSA” (የ Every Student Succeeds Act (የእያንዳንዱ ተማሪ ስኬታማነት አዋጅ)) በመባል የሚታወቀው የፌደራል ትምህርት ህግ ፣ በቅርቡ በማደጎ ውስጥ ላሉ ህጻናት የመጀመሪያ ትምህርት ቤት፣ የመጓጓዣ እና የአፋጣኝ ምዝገባ ጥበቃዎችን የሚሰጥ ክፍል ጨምሯል። በማደጎ ውስጥ ያለ ልጅን የሚንከባከቡ ከሆነ፣ የልጅዎን ትምህርት ለመደገፍ እንዴት እንደሚረዱዎት የዲስትሪክትዎን “Foster Care Liaison (የማደጎ ህብረት)” ለማነጋገር ይጠይቁ።
ከ Treehouse for Kids (የልጆች የዛፍ ቤት) (https://www.treehouseforkids.org/) በሚገኘው Guide to Supporting Students in Foster Care (በማደጎ ውስጥ ያሉ ተማሪዎችን የሚደግፉበት መመሪያ) ስለ ጥበቃዎች እና ድጋፎች፣ ከ OSPI Foster Care Program (የማደጎ ፕሮግራም) (https://www.k12.wa.us/student-success/access-opportunity-education/foster-care)፣ እና በቀጥታ ሊንክ፦ https://www.treehouseforkids.org/wp-content/uploads/2018/01/
treehouse2017final2ndedinteractive.pdf የበለጠ ያንብቡ።የትምህርት ቤት ምርጫ አማራጮች እና ወደ ሌላ ዲስትሪክት መዘዋወር
በከተማችን ብዙ አይነት የህዝብ ትምህርት ቤት አማራጮች አሉ። በዲስትሪክትዎ ውስጥ ያልሆነ ነገር ግን በአቅራቢያው ባለ ዲስትሪክት ወይም በኦንላይን ያለውን አማራጭ ለማግኘት ከፈለጉ፣ ስለ "ነዋሪ ያልሆኑ ዝውውር"- ማለትም ለተማሪዎ ከዲስትሪክቱ ውጭ ያሉ አገልግሎቶችን ስለመፈለግዎ ከዲስትሪክቱ ጋር ለመነጋገር መጠየቅ ይችላሉ-።
እያንዳንዱ ዲስትሪክት “ነዋሪ ያልሆኑ” ወይም “የምርጫ” ዝውውሮችን በተመለከተ ፖሊሲ ሊኖረው ይገባል። ከአንዱ ዲስትሪክት ወደሌላ ለመዘዋወር መጠየቅ ባለ ሁለት ደረጃ ሂደት አለው፣ የሚኖሩበት ዲስትሪክት ተማሪዎን መልቀቁን እና ነዋሪ ያልሆነው ዲስትሪክት ተማሪዎን መቀበሉን ይጠይቃል። በ OSPI ድረገጽ፣ https://www.k12.wa.us/student-success/support-programs/student-transfers በኦንላይን ምርጫ የዝውውር ጥያቄ ፖርታል ላይ ሊንክ ወይም ዲስትሪክትዎን ይጠይቁ። ለበለጠ መረጃ የእኛን የትምህርት ቤት ምርጫ / የዝውውር ድረገፅ፣ የምርጫ ዝውውር መሳሪያ እና የ OSPI በተማሪዎች ዝውውር ድረገጽ ላይ ይመልከቱ።
በዋሽንግተን ግዛት ውስጥ ካሉት አንዳንድ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች አማራጮች መካከል፡-
የኦንላይን እና የቤት/የትምህርት ቤት አጋርነቶችን ጨምሮ አማራጭ የመማሪያ ተሞክሮዎች፦
አንዳንድ የትምህርት ቤት ዲስትሪክቶች አንዳንድ ወይም ሁሉም መመሪያዎች ከመደበኛ ክፍል ውጭ የሚሰጡበት “አማራጭ የመማሪያ ተሞክሮዎች” የህዝብ ትምህርት አይነት ይሰጣሉ። ይህ የኦንላይን ትምህርት ቤት፣ እና የቤት/የትምህርት ቤት አጋርነት ፕሮግራሞችን ያካትታል።
በአካባቢዎ ስላሉት አማራጭ አማራጮች መረጃ ለማግኘት የትምህርት ቤት ዲስትሪክት ቢሮዎን ይጠይቁ ወይም የዲስትሪክቱን ድረ-ገጽ ይመልከቱ።
እንዲሁም የጸደቁ የኦንላይን ትምህርት ፕሮግራሞችን ዝርዝር በ OSPI የመማሪያ አማራጭ ድረገጾች፦ https://ospi.k12.wa.us/student-success/career-technical-education-cte/cte-skill-centers እዚህ ማግኘት ይችላሉ።
ክልላዊ የክህሎት ማዕከላት፦
የክህሎት ማዕከላት ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የተለያዩ የሙያ እና የቴክኒክ ፕሮግራሞች ትምህርቶችን የሚያቀርቡ ክልላዊ ፕሮግራሞች ናቸው። በግዛቱ ዙሪያ በጣም ብዙ የክልል የክህሎት ማዕከላት፣ እና በርካታ የቅርንጫፍ ካምፓሶች አሉ። ዲስትሪክትዎ በክህሎት ማዕከል ፕሮግራም ውስጥ መሳተፉን፣ እና ምን አይነት ኮርሶችን እንደሚሰጡ ለማየት ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አማካሪዎ ወይም ከዲስትሪክቱ ቢሮ መረጃን ይጠይቁ።
የክህሎት ማዕከላት ዝርዝር፣ እና የድረገጻቸውን ሊንኮች፣ በ OSPI የሙያ እና ቴክኒካል ትምህርት ገጽ ላይ፣ https://ospi.k12.wa.us/student-success/career-technical-education-cte/cte-skill-centers እዚህ ማግኘት ይችላሉ።
የ Open Doors Re-Engagement ፕሮግራሞች፦
ብዙ ወረዳዎች እድሜያቸው ከ 16-21 የሆኑ ተማሪዎችን የሚደግፉ የ Open Doors Youth Reengagement (የእድሎች የታዳጊ የድጋሚ ተሳትፎ) ፕሮግራሞችን አዘጋጅተዋል፣ ነገር ግን እንደገና መሞከር ይፈልጋሉ። የ Open Doors ፕሮግራሞች ብዙ ጊዜ ተለዋዋጭ መርሃ ግብሮች አሏቸው፣ እና ከእያንዳንዱ ታዳጊ ጋር ተቀራርበው ወደ ምርቃት እና ለስኬት የሚያደርሱበትን መንገድ ያዘጋጃሉ። ወደ ትምህርት ቤት የሚመለሱበት ወይም ወደ ትክክለኛው መንገድ የሚመለሱበት አማራጭ መንገድ እየፈለጉ ከሆነ በአጠገብዎ የ Re-engagement (የድጋሚ ተሳትፎ) ፕሮግራም ካለ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አማካሪዎን ወይም በዲስትሪክት ቢሮ ውስጥ ያለን ሰው ይጠይቁ።
እንዲሁም አማራጮችን እንዲያገኙ ልንረዳዎት ስለምንችል ያነጋግሩን። በ 1-866-297-2597 ይደውሉልን፣ በ oeoinfo@gov.wa.gov ኢሜይል ያድርጉልን፣ ወይም በኦንላይን የመቀበያ ሲስተም በ፦ https://services.oeo.wa.gov/oeo ያግኙን።
ሌሎች የህዝብ ትምህርት ቤት አማራጮች
በዋሽንግተን የትምህርት ዲስትሪክቶች ከሚተዳደሩ 295 ትምህርት ቤቶች በተጨማሪ፣ በዋሽንግተን ግዛት ውስጥ ያሉ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች አማራጮች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦
የ State School for the Blind፣ እና የ State School for the Deaf፣ የጎሳ ትምህርት ቤቶች፣እና የሕዝብ ቻርተር ትምህርት ቤቶች።በ Spokane Public Schools (የስፖኬን የሕዝብ ትምህርት ቤቶች) ለተፈቀዱ ቻርተር ትምህርት ቤቶች፣ እዚህ ይመልከቱ፦ here:https://www.spokaneschools.org/page/charter-school-authorization።
የእኛን የትምህርት ቤት ምርጫ / የዝውውር መሳሪያ እና በተማሪዎች ዝውውር ላይ የ OSPI ድረገጽን https://www.k12.wa.us/student-success/support-programs/student-transfers፣ ለበለጠ መረጃ ይመልከቱ።
ስለ የጎሳ ትምህርት ቤቶች መረጃ በ OSPI የ Office of Native Education (የሃገር ውስጥ ትምህርት ቢሮ) ድህረ ገጽ በ፦ https://www.k12.wa.us/student-success/access-opportunity-education/native-education/types-tribal-schools ላይ ያገኛሉ።
በአሁኑ ጊዜ ስለሚሰሩ የህዝብ ቻርተር ትምህርት ቤቶች መረጃ ከ Washington Charter School Commission (የዋሽንግተን ቻርተር ትምህርት ቤት ኮሚሽን) በኦንላይን በ፦ https://charterschool.wa.gov/ ላይ ያገኛሉ። በኮሚሽኑ የተፈቀደላቸው እና አሁን እየሰሩ ያሉ የቻርተር ትምህርት ቤቶች ዝርዝር ለማግኘት እዚህ፦ https://charterschool.wa.gov/our-charter-public-schools/ ላይ ይመልከቱ።