በ 2006፣ ቤተሰቦችን፣ ተማሪዎችን፣ መምህራንን እና ማኅበረሰቦችን የሕዝብ ትምህርት ቤቶችን K-12 ትምህርት ሥርዓት እንዲረዱ በማገዝ እና የሚያጋጥሙ አሳሳቢ ነገሮችን በጋራ መፍትሔ በመስጠት ያለውን የትምህርት ዕድል የማግኘት ክፍተት ለማጥበብ እንዲቻል የ Washington State Legislature (የዋሽንግተን ስቴት ሕግ አውጪ ምክር ቤት) House Bill 3127 የተባለውን Office of the Education Ombuds (OEO) (የትምህርት እንባ ጠባቂ ጽሕፈት ቤትን) ማቋቋሚያ አዋጅ አውጥቷል። ከሕዝብ ትምህርት ቤቶች ሥርዓት ራሳችንን ነጻ ማድረጋችንን ማረጋገጥ እንዲቻል ሕግ አውጪው ምክር ቤት እኛን በአገረ ገዢው ጽሕፈት ቤት ሥር እንድንሆን አድርጎናል።
ያሉን ግብዓቶች ውስን ስለሆኑ በ እኛ ስትራቴጂያዊ ዕቅድ ሥር የሚወድቁ ችግሮችን ለመደገፍ እና እንደ በትብብር ችግር ፈቺዎች በተማሪ ተሞክሮ ላይ በየትኛው ቦታ ላይ አዎንታዊ ተፅዕኖ ሊኖረን እንደሚችል ለይቶ በማወቅ የእኛን የእንባ ጥበቃ ድጋፍ አሰጣጥ እንደ አስፈላጊነቱ ቅድሚያ ተሰጪ እንዲሆን አድርገናል። OEO ቁጥራቸው ከ7 በማይበልጥ የሙሉ ጊዜ ሠራተኞች እየታገዘ በመላው ስቴቱ ሥራውን ይሠራል።
የኛ ኃላፊነቶች
- ስለ K-12 የሕዝብ ትምህርት ሥርዓት ያሉትን አሳሳቢ ነገሮች በተመለከተ የሚሰጡ አስተያየቶችን ማዳመጥ እና ለጥያቄዎች ምላሽ መስጠት
- የትብብር ችግር አፈታት ዘዴን ለመደገፍ እና ፍትሐዋኢ ትምህርት አሰጣጥን ለማስፈን መደበኛ ያልሆነ የግጭት አፈታት ዘዴን መጠቀም
- ስለ ቤተሰብ እና ማኅበረሰብ ተሳትፎ እና የሥርዓት ማስከበር ሙግቶች የግል ሥልጠና፣ ማሰለጫ ዘዴዎችንና እገዛዎችን እንዲሁም የተግባር ሥልጠና መስጠት
- የእኛን የትምህርት ፖሊሲ ጥብቅ ምክሮችን ለማዘጋጀት ውሂብ መሰብሰብ እና አዝማሚያዎችን ለይቶ ማወቅ