በዋሽንግተን K-12 የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ተማሪን የሚነካ ጥያቄ ወይም ስጋት

የእኛን እገዛ ያግኙ:

Black and White Icon of electronic device sending message. Created by Priyanka from Noun Projectበበይነመረብ – የእኛን አዲሱን የበይነመረብ መመዝገቢያ ሂደት እንዲጠቀሙ እናበረታታዎታለን።  በእርስዎ ስም እና በሚሠራ የኢሜይል አድራሻ ተጠቅመው የራስዎትን መለያ መፍጠር ይኖርብዎታል።  መለያ ከፈጠሩ እና የበይነመረብ መመዝገቢያ ሂደት አሟልተው ካጠናቀቁ በኋላ፣ መረጃ ለእርስዎ ለመስጠት ወይም ቀጠሮ ለማስያዝ በተቻለ ፍጥነት የሆነ ሰው እርስዎን አግኝቶ ያነጋግርዎታል።  የእኛ የበይነመረብ መመዝገቢያ በማናቸውም ጊዜ ሊገኝ ይችላል፣ ሆኖም ግን የሆነ ሰው ክትትል የሚያደርገው በመደበኛ የሥራ ሰዓታት ) ብቻ ነው።

የስራ ሰዓታት

ሰኞ 8:00 a.m. – 6:00 p.m.

ማክሰኞ 8:00 a.m. – 4:00 p.m.

ረቡዕ 8:00 a.m. – 4:00 p.m.

ሐሙስ 8:00 a.m. – 6:00 p.m.

ዓርብ 8:00 a.m. - 6:00 p.m.

Calendar by ghufronagustian from NounProject.comየመግቢያ ቀጠሮ ያስይዙ -  ጊዜ ይቅጠሩ ጊዜ ይቅጠሩ ተቀባይ ባለሙያ እንዲደውልሎት፣ አስፈላጊ መረጃዎችን እንዲሰበስብ እና ስለ ጥያቄዎ ወይም ሁኔታዎ እንዲያማክሮት።እንደ አማራጭ፣ የሚያስፈልግዎትን መረጃ በሚመችዎት ጊዜ  በቀጥታ መስመር የቅበላ ሂደትን በመጠቀም.ማጠናቀቅ ይችላሉ።

Black and white icon of mobile phone making a call. Created by Thays Malcher from Noun Project.በስልክ – የሆነ ግለሰብን በግል ለማነጋገር ከመረጡ ወይም የበይነመረብ መመዝገቢያ ሂደቱ ላይ እገዛ ካስፈለግዎት፣ በእኛ የሥራ ሰዓታት ከሰኞ እስከ ዓርብ ከ  በነጻ የስልክ መሥመር 1-866-297-2597 ላይ እባክዎ ይደውሉልን። የእኛ ሠራተኞች ከ150 በሚበልጡ ቋንቋዎች የስልክ አስተርጓሚ አገልግሎትን ማግኘት ይችላሉ።

Black and white icon of envelope with two papers inside. The first paper has the "at" email icon. The second paper has lines for writing a letter. Created by Anang Taufik from Noun Project.በ ፋክስ ወይም በኢሜይል – ለእንባ ጥበቃ አገልግሎቶች ጥያቄ ማቅረብ ቅጽን ያውርዱ እና የተሞላውን ቅጽ በፋክስ፣ በፖስታ ወይም ኢሜይል ወደ OEO ይላኩት (መላኪያ አድራሻው በቅጹ ላይ ታትሟል።  ፋክስ፦ 1-844-886-5196


የፍቃድ ቅጾች

ትምህርት ቤትን ለማነጋገር የሚሰጥ ፈቃድ ከ Ombuds ጋር የሚሠሩ ከሆነ እና ለ OEO የተማሪውን ሁኔታ በተመለከተ በቀጥታ ከትምህርት ቤቱ እና ከዲስትሪክቱ ሠራተኞች ጋር እንደ ተገቢነቱ እንዲነጋገር ፈቃድ ለመስጠት የሚፈልጉ ከሆነ ትምህርት ቤትን ለማነጋገር የሚሰጥ ፈቃድ ቅጽን እባክዎ ያውርዱ፣ ይሙሉት እና መልሰው ያስገቡት።

የተማሪ መረጃ መዝገብን መጠየቂያ ቅጽከ Ombuds ጋር የሚሠሩ ከሆነ፣ አሳሳቢዎቹን ነገሮች የተሻለ ለመረዳት የእርስዎን ልጅ የትምህርት ቤት መዛግብት ማየት ያስፈልግዎት ይሆናል።  ያንን ማድረግ ካስፈለገን፣ ትምህርት ቤቱ ሪኮርዶቹን እንዲሰጠን የእርስዎን ፈቃድ በኋላ ላይ እንጠይቅዎታለን።  ይህን ቅጽ የምንጠቀመው ለኛ መዛግብቶች ለሕዝብ ይፋ ለማድረግ ነው፦  የተማሪ መረጃ መዝገብን መጠየቂያ ቅጽ

  • እነዚህን ቅጾች በበይነመረብ መመዝገቢያ ሂደቱ፣ ወይም በፋክስ፣ ወይም በኢሜይል ማስገባት ይችላሉ።

ለጥያቄዎ ወይም የሚያሳስብዎት ነገር እገዛ ማግኘት:

በበይነመረብ፣ ወይም በስልክ፣ በፋክስ ወይም በኢሜይል እባክዎ እኛን ያነጋግሩን።  OEO ውስን ሠራተኞች እና ገንዘብ እንዳለው እና ይህም በመሆኑ ባለው ስትራቴጂያዊ ዕቅድ መስፈርት መሠረት ነገሮችን እንደ አንገብጋቢነታቸው ቅድሚያ እየሰጠ እንደሚሠራ እባክዎ ልብ ይበሉ።

መደበኛ ያልሆነ የግጭት አፈታት ዘዴ

OEO ስለ ዋሽንግተን K-12 የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ጥያቄዎች ወይም የሚያሳስቡት ነገሮች ያሉትን ማናቸውንም ሰው ያግዛል። መረጃ፣ ሪፈራል፣ የመሣሪያ ኪት እና ሌሎች ግብዓቶችን ለእርስዎ ልንሰጥዎት እንችላለን።

የOEO ሕጋዊ ተልዕኮ ያለውን የትምህርት ዕድል ክፍተት መቀነስ ነው። የኛ ስልታዊ ዕቅድ ቅድሚያ ተሰጪ ጉዳዮች በትምህርታዊ ፍትሕ፣ በተለይም በኮቪድ-19 ይበልጥ በተጎዱ ማኅበረሰቦች ላይ ያተኩራሉ። እንደ መደበኛ ያልሆነ ሽምግልና እና ሥልጠና የመሳሰሉ የእኛን ውስን የግጭት አፈታት ግብዓቶች በ K-12 ተማሪዎች ላይ እንዲያተኩሩ እያደረግን ያለን ሲሆን ይህም፦

  • በከፊል የትምህርት ቀናትን አክብረው እንዲገኙ የተፈቀደላቸው የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎችን ጨምሮ ከትምህርት ቤት ውጭ ያሉ ተማሪዎች
  • ነጭ ያልሆኑ ሰዎች፣ ጥቁሮች ወይም ቀይ ህንዶች 
  • የመኖሪያ ቤት እጦት ችግር ላይ ያሉ
  • በዘመድ ወይም በማደጎ እንክብካቤ ሥር ያሉ 
  • በወጣት አጥፊ ማረሚያ ወይም በወጣት አጥፊ መልሶ ማቋቋሚያ ሥርዓቶች ውስጥ ያሉ
  • ስደተኛ፣ ፍልሰተኛ፣ ጥገኛ፣ ወይም ማይግራንት፣ ወይም የመጀመሪያ ቋንቋ(ቸው) እንግሊዝኛ ያልሆኑ ተማሪዎች ወይም ቤተሰቦች፣ ወይም
  • Wraparound with Intensive Services (WISe፣ ራፕአራውንድ ከልዩ አገልግሎቶች ጋር) ወይም Children’s Long Term Inpatient Programs (CLIP፣ የልጆች የረዥም ጊዜ ታካሚዎች ፕሮግራም) ድጋፍ የሚያገኙ

በተጨማሪ መምህራንን እና የማኅበረሰብ መብት ተሟጋቾችን ተማሪዎችን እንዲያግዙ እና ግጭቶችን እንዲፈቱ ልናሠለጥናቸው እንችላለን። 

ይህን እገዛ ለማግኘት እባክዎ ኢሜይል ወደ oeoinfo@gov.wa.gov ይላኩ ወይም ወደ 1-866-297-2597 ይደውሉ።  ከእኛ ቡድን አባላት አንዱ ለጥያቄዎች ብዙውን ጊዜ በኢሜይል ወይም አጭር ጊዜ በሚወስድ የስልክ ጥሪ ምላሽ መስጠት ይችላል። ከቤተሰቦች፣ ተማሪዎች፣ መምህራን እና ሌሎች የማኅበረሰብ ባለ ድርሻ አካላት የሚቀርቡ አሳሳቢ ነገሮች ጥቆማን እና ጥያቄዎችን በደስታ ተቀብለን እናስተናግዳለን።የእኛ ጽሕፈት ቤት ቤተሰቦች እና ትምህርት ቤቶች ግጭቶችን መፍታት እንዲችሉ ለማገዝ በትብብር፣ መደበኛ ባለሆነ መንገድ፣ እና በምስጢር፣ እንሠራለን። 

ስለ እኛ ምን ማወቅ ይኖርብዎታል?

ይህ አጭር ሰነድ እንዴት ከቤተሰቦች ጋር እንደምንሠራ ያብራራል እኛ ለማገዝ ምን ማድረግ እንደምንችል እና እንደማንችል ለመረዳት እንዲያነቡት እናበረታታዎታለን።

እነዚህ ሰነዶች መምህራንን እና በማኅበረሰቡ ውስጥ ያሉ ልሂቃንን እንዴት ማገዝ እንደምንችል ያብራራሉ።