የ OEO የሕግ አውጪ ተልዕኮው የዕድል ክፍተቶችን ለመቀነስ ነው። የስትራቴጂክ እቅዳችን ውስን የግጭት አፈታት ሀብቶቻችንን ለምሳሌ መደበኛ ያልሆነ ሽምግልና እና ስልጠናን በሚከተሉት K-12 ተማሪዎች ላይ በማተኮር የእድል ክፍተቱን ለመቀነስ ቅድሚያ ይሰጣል፦
- በከፊል የትምህርት ቀናት የሚያገኙ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎችን ጨምሮ ከትምህርት ውጪ የሆኑ
- ቀለም ያላቸው፣ ጥቁሮች ወይም የአገሬው ተወላጅ የሆኑ
- የቤት እጦት እያጋጠማቸው ያሉ
- በዘመድ ወይም በማደጎ ውስጥ ያሉ
- በወጣት ፍትህ ወይም በወጣት ማገገሚያ ስርዓቶች ውስጥ የተሳተፉ
- አዲስ መጤ፣ ስደተኛ፣ ጥገኝነት ፈላጊ ወይም ጊዜያዊ ስደተኛ፣ ወይም የመጀመሪያ ቋንቋቸው እንግሊዘኛ ያልሆኑ ተማሪዎች ወይም ቤተሰቦች
- በተጠናከሩ አገልግሎቶች የተጠቀለለ (WISe) ወይም የልጆች የረጅም ጊዜ የተኝቶ ታካሚ ፕሮግራሞች (CLIP) ድጋፎችን እየተቀበሉ ያሉ፣ ወይም
- ፆታ የቀየሩ ወይም ፆታ የሌላቸው ወጣቶች