Individualized education program ወይም “IEP” ምንድነው?

Individualized education program ወይም “IEP” ምንድነው?

Individualized Education Program (IEP፣ ግለሰባዊ የትምህርት ፕሮግራም) አካል ጉዳተኛ ተማሪ ትርጉም ያለው ትምህርት እንዲያገኝ የሚያስፈልገውን መመሪያ እና አገልግሎት የሚዘረዝር መግለጫ ነው። Individualized education program፣ ወይም IEP፣ ተማሪው ስለሚቀበለው ልዩ ትምህርታዊ አገልግሎቶች የሚገልጽ ሰነድ ነው። IEP ህጋዊ ሰነድ ሲሆን ተማሪዎች በ IEP የተዘረዘሩትን አገልግሎቶች የማግኘት መብት አላቸው። IEP ለልጁ እና ለትምህርት ፍላጎቶቹ የተዘጋጀ መሆን አለበት፣ እንዲሁም አገልግሎቶችን ለማድረስ የፈጠራ ስልቶችን ሊያካትት ይችላል።

IEP ማካተት ያለበት፦

 • የተማሪው የአሁን የትምህርት እና የተግባር አፈጻጸም ደረጃዎች ተማሪው እንዴት እየሰራ እንዳለ የሚያሳይ መግለጫ
 • አመታዊ የትምህርት ግቦች
 • የልጁ እድገት እንዴት እንደሚለካ እና የልጁ መሻሻል ሪፖርት በየጊዜው የሚቀርብበት ሰነድ
 • አንድ ልጅ በሁለቱም አጠቃላይ ትምህርታዊ የክፍል ቅንብር እና ልዩ ትምህርታዊ ቅንብር የሚቀበላችውን ሁሉም አገልግሎቶች ይገልጻል።
 • እንደ የንግግር እና የቋንቋ ቴራፒ፣ መጓጓዣ፣ እና የምክር አገልግሎት የመሳሰሉ ተማሪው የሚቀበላቸው “ተዛማጅ አገልግሎቶች” መግለጫ
 • እንደ የተሻሻለ ማንበቢያ መሳሪያዎች፣ የፈተና ማንበቢያ እና ለሎች ግምገማዎች፣ ለትምህርት የሚሆኑ መቅጃዎች፣ የመሳሰሉት ሊቀርቡ ስለሚገባቸው ሁሉም የፕሮግራም ማሻሻዎች መግለጫ
 • ተማሪው አጋዥ የተክኖሎጂ መሳሪያዎች እና አገልግሎቶች እንደሚያስፈልገው መወሰን። አጋዥ ተክኖሎጂ ማለት የተማሪውን አቅም የሚያሳድጉ ወይም የሚጠብቁ እና እንደ ኮምፒውተር ወይም ኪቦርድ ያሉ በገበያ የሚመረቱ ነገሮችን የሚያካትቱ መሳሪያዎች ወይም ስርዓትቶች ማለት ነው።
 • ለምቹ PE ብቁ የመሆን ውሳኔ፣ እና ብቁ ከሆኑ፣ እንዴት ይሰጣል
 • ተማሪው በአጠቃላይ የትምህርት ክፍሎች እና እንቅስቃሴዎች እንደት እንደሚሳተፍ፣ እና ይህ ካልሆነ፣ ለምን የሚለውን የሚገልጽ
 • በ IEP ቡድን አስፈላጊ ከሆነ፣ ለተማሪው ማንኛውንም የተራዘመ የትምህርት ዘመን አገልግሎቶችን ማመቻቸት
 • ለተማሪው የሚያስፈልግ ከሆነ ጣልቃ መግባት
 • ለሚቀርቡት አገልግሎቶች ቦታ፣ ጊዜ እና ድግግሞሽ
 • አገልግሎት የሚጀምርባቸው ቀናት
 • በ IEP ቡድን አስፈላጊ ተብሎ ከተወሰነ ተማሪው 16 አመት ሲሞላው፣ ወይም ከዚያ በታች ከሆነ IEP ዘግይቶ ተግባራዊ መሆን ይጀምራል፦ 1) ከሁለተኛ ደረጃ በኋላ ሊለኩ የሚችሉ ግቦች 2) ተማሪው እነዚህ ግቦች ላይ እንዲደርስ ለመርዳት የሚያስፈልጉ የሽግግር አገልግሎቶች

በተጨማሪም፣ ተቀያሪ መመዘኛዎችን የሚወስዱ ተማሪዎች የሚከተሉትን በእነርሱ IEP ማካተት አለባቸው፦

 • የተቀያሪ ወይም የአጭር ጊዜ አላማዎች መግለጫ
 • ተማሪው በመደበኛ ምዘና ለምን መሳተፍ እንደማይችል የሚያስረዳ መግለጫ
 • ለተማሪው የተለየ ተቀያሪ ምዘና ለምን እንዳስፈለገው የሚያስረዳ መግለጫ

ልጄ ለልዩ ትምህርት ብቁ ከሆነ ወይም ከሆነች ከመጀመሪያው መመዘኛ በኋላ በምን ያህል ፍጥነት IEP ማግኘት ይችላል ወይም ትችላለች?

ተማሪው ለልዩ ትምህርት ብቁ መሆኑ በተወሰነ በ 30 ቀን ውስጥ፣ የ IEP ስብሰባ መጠራት አለበት። የትምህርት ቤቱ ዲስትሪክት ተማሪው አንዴ ለልዩ ትምህርት ብቁ መሆኑን ከወሰነ፣ ዲስትሪክቱ የ IEP ስብሰባ ለማድረግ እና ለተማሪው የግል እቅድ ለማውጣት 30 ቀናት (የትምህርት ቀናት አይደሉም) አለው።

IEP የሚያዘጋጀው ማን ነው?

የ IEP ቡድን የተመሰረተው የተማሪውን የትምህርት ፕሮግራም ለማዘጋጀት መርዳት በሚችሉ ሰዎች ነው። የቡድኑ ሰዎች IEP ውን የመጻፍና ማጽደቅ ሃላፊነት አለባቸው። የሚከተሉት የ IEP ቡድኑ ሰዎች እና ሁሉም የ IEP ስብሰባዎች ላይ በአጠቃላይ መገኘት አለባቸው።

 • ወላጅ ወይም ሞግዚት
 • ከተማሪው አጠቃላይ ትምህርት አስተማሪዎች ቢያንስ አንዱ (ተማሪው በአጠቃላይ የትምህርት አካባቢ ውስጥ ከሆነ ወይም እየተሳተፈ ከሆነ)
 • ከተማሪው የልዩ ትምህርት አስተማሪዎች ቢያንስ አንዱ ወይም፣ ተገቢ ሲሆን፣ ልዩ ትምህርት አቅራቢ
 • በአካል ጉዳተኛ ልጆች ትምህርት ብቁ የሆነ እና ስለ አጠቃላይ ስርአተ ትምህርትና ስላለው ግብአቶች (እንደ ልዩ ትምህርት ዳይሬክተር ያሉ) ብቃት ያለው የዲስትሪክቱ ተወካይ
 • የግምገማን መረጃ መተርጎም የሚችልግለሰብ (ከላይ ከተጠቀሱት ሰዎች አንዱ ወይም የትምህርት ቤቱ የስነ ልቦና ባለሙያ ሊሆን ይችላል)
 • በወላጅ ወይም በዲስትሪክቱ ውሳኔ፣ ሌሎች እውቀት ያላቸው ወይም በልጆች ዙሪያ ልዩ ባለሙያ
 • ተማሪው (ተገቢ ከሆነ)
 • የሽግግር አገልግሎት አቅራቢዎች (የሙያ ስፔሻሊስቶች ወይም ከኤጀንሲው ውጪ ያለ ሰው እንደ Division of Developmental Disabilities (DDD፣ የእድገት አካል ጉዳት ክፍፍል))።

ሌሎች ሰዎች በ IEP ቡድን ሊኖሩ ይችላሉ። ህጉ በልዩነት “እውቀት ያላቸውን ወይም ልጆች ዙሪያ ያሉ ልዩ ኤክስፐርቶች” በ IEP እንዲሳተፉ ይፈቅዳል። ይሀ ማለት የ IEP ቡድኑ ዘመዶችን፣ ቤተሰቦችን፣ጓደኞችን፣የህብረተሰቡን አባላት፣ተራፒስቲች፣ እና ጠበቆችን ያካትታል። ዲስትሪክቱ ወይም ቤተሰብ እውቀት ያለው ወይም በልጁ ዙሪያ ኤክስፐርት የሆነ ሰው ይወስናል። በልጅዎ IEP ቡድን ውስጥ ሌሎች ሰዎች እንዲካተቱ ከፈለጉ፣ እንዲጋበዙ ለትምህርት ቤቱ መንገርዎን እርግጠኛ ይሁኑ። ነገር ግን፣ በ IDEA እና በከተማው ልዩ ትምህርት ህግ ስር፣የ IEP ቡድን አባላት በማንኛውም ሁኔታ እንዲገኙ ላያስፈልግ ይችላል። ከላይ የተዘረዘው የ IEP ቡድኑ አባላቱ የትምህርት ዘርፍ የስብሰባው ርእሰ ጉዳይ እና ወላጁ እና የትምህርት ቤቱ ዲስትሪክት የእሱ ወይም የእሷ መገኘት አስፈላጊ እንዳልሆነ በጽሁፍ ከተስማሙ በ IEP ስብሰባ ላይ እንዲሳተፉ አይገደዱም። ለምሳሌ፣ የንግግር አገልግሎቶች የ IEP ስብሰባ ርእሰ ጉዳይ ካልሆነ እና ስብሰባው ስለ ተማሪው የባህሪ ጣልቃገብ እቅድ ብቻ መወያየት ከሆነ ወላጅ እና የትምህርት ቤት ዲስትሪክት የንግግር እና የቋንቋ አቅራቢ እንዲገኝ ላያስፈልግ ይችላል ብለው በጽሁፍ ከተስማሙ መገኘት አያስፈልጋቸውም። በተጨማሪ፣ ወላጅ እና የትምህርት ቤቱ ዲስትሪክት በጽሁፍ ከተስማሙ ስብሰባው የቡድኑን አባል ቦታ ማሻሻያ ወይም ውይይትን የሚያካትት ቢሆንም የ IEP ቡድን አባላት በስብሰባው ላይገኙ ይችላሉ፣ ነገር ግን ያልተገኘው የቡድን አባል ከስብሰባው በፊት ለወላጅ እና ለትምህርት ቤቱ ዲስትሪክት ለ IEPው እድገት የጽሁፍ ግብአት ማስረከብ አለበት።

የ IEP ቡድኑ ስብሰባ መቼ እንደሆነ እንዴት ማወቅ እችላለሁ?

ዲስትሪክቱ ለወላጆች የ IEP ስብሰባ አላማን፣ ጊዜውና ቦታውን፣ እና ማን እንደሚሳተፍ ማሳወቅ አለባቸው። ወላጆች የመሳተፍ እድል እንዲያገኙ ዲስትሪክቱ ቀደም ብሎ ማሳወቁን እርግጠኛ መሆን አለበት። ስብሰባው በሰአት እና በቦታ ስምምነት መታቀድ አለበት። ወላጅ እና ዲስትሪክቱ ከተስማሙ፣ ስብሰባው በስልክ ወይም በቪዲዮ ስብሰባ መሆን ይችላል።

ለ IEP ምን አስተዋጾ ማበርከት እችላለሁ?

ስኬታማ ልዩ የትምህርት ፕሮግራም ለመፍጠር ከወላጅ እና ከሌሎች ተማሪውን ከሚያውቁ እና ስለ እሱ ወይም እሷ ስኬት የሚያስቡ ሰዎች ግብአት ቁልፍ ነው። ወላጆች በ IEP ቡድኑ ዋና ክፍል የሆኑ እና ሌሎች ጠቃሚ ሰዎችን ለማጠቃለል አንዳንድ ትልልቅ ሃሳቦች ይኖራቸዋል። በ IEP ቡድኑ እቅድ በሚያወጡበት ጊዜ አንዳንድ እገዳዎችን ማስተዋል አለባቸው። በሂደቱ አስተዋጽኦ ይኖራቸዋል ብለው የሚያስቧቸውን ሌሎች ሰዎች ለትምህርት ቤቱ ማሳወቅ አለቦት። እንደ ጠበቃ የእርሶ ዋና ሚና ትምህርት ቤቱ ዲስትሪክት የሚሰጠውን የትምህርት ፕሮግራም እና አገልግሎቶች መመዘን ነው። ለምሳሌ፣ ስለ ልጅዎ አቅም ካልዎት ግንዛቤ አንጻር ግቦቹ እና አላማዎቹ ምክንያታዊ ናቸው? በዲስትሪክቱ የሚሰጡት የአገልግሎቶች አይነቶች ለልጅዎ ልዩነት ይፈጥራሉ? የትምህርት እቅዱን ለማሻሻል አስተያየት ካልዎት በ IEP ቡድኑ ስብሰባ ላይ መናገር ይችላሉ።[ አዲስ እይታ እና ፈጠራ በሂደቱ መጨመር ይችላሉ።  ልጅዎ የሚሳተፍበትን አስተማሪዎች ያላስተዋሉትን መንገዶች ያስቡ። ለምሳሌ፣ ልዩ እንቅስቃእሴ ወይም የስፖርት ጊዜ ሽልማት ልጅዎን በቤት ውስጥ ስራዎችን እንዲሰራ የሚያነሳሳ ከሆነ፣ ትምህርቱንም ለመጨረስ ሽልማት መስጠት ይቻላል። ወይም ልጅዎ ብዙ ሰው ሲኖር፣ እና በጫጫታ የሚረበሽ መሆኑን የሚያውቁ ከሆነ ልጅዎ ከሌሎች ተማሪዎች በፊት ወይም በኋላ ክፍሎች እንዲቀይር ሃሳብ መስጠት ይችላሉ።

IEPው የባህሪ ችግሮችን እንዴት ይፈታል?

የባህሪ ችግሮች ካሉ IEP የተግባር ግምገማ እና የባህሪ ጣልቃገብነት እቅድ ማካተት ይኖርበታል። ባህሪው በሚማርበት ወይም በለሎች ተማሪዎች ላይ ተጽእኖ ካደረገ፣ IEP ባህሪን ለማሻሻል ግቦችን እና አላማዎችን ማቅረብ እና ችግሩን ለመፍታት ስልቶችን መስጠት አለበት። የተማሪው ባህሪ ከአካል ጉዳቱ ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል ማታወስ አስፈላጊ ነው። IEP የባህሪ ችግሮችን አስቀድሞ ማወቅ እና ችግሮቹ ከመከሰታቸው በፊት ምላሽ ለመስጠት ውጤታማ መንገዶችን መፍጠር አለበት።

IEP የሚከለሰው ወይም የሚገመገመው መቼ ነው?

ቢያንስ በአመት አንዴ፣ ነገር ግን በብዛት የ IEP ቡድን አባል ሲጠየቅ ነው። IEP ቢያንስ በአመት አንዴ መገምገም አለበት። ሆኖም፣ የግምገማ ጊዜው ቢያልፍም ዲስትሪክቱ IEPውን መከተል አለበት። በአመቱ መጨረሻ፣ የ IEP ቡድን የትምህርት ፕሮግራሙን ለመገምገም እና አመታዊ ግቦቹ መሳካታቸውን ለማወቅ መገናኘት አለባቸው። ተማሪው የትምህርት እድገት ካሳየ ወይም ስለ ተማሪው አዲስ መረጃ ከቀረበ IEP መከለስ አለበት። IEP በተጨማሪ ተማሪው ሲያድግ የሚለወጡ ፍላጎቶችን አስቀድሞ መገመት አለበት። IEP በማንኛውም ጊዜ በቡድን አባል ጥያቄ ሁኔታዎች ሲቀየሩ ሊገመገም ይችላል። ነገር ግን፣ በ IDEA እና በከተማው የልዩ ትምህርት ህግ፣ ወላጆች እና ዲስትሪክቱ ይሀን ለማድረግ ከተስማሙ የ IEP ስብሰባ ሳይጠሩ ከአመታዊው ግምገማ ብኋላ በ ልጁ IEP ላይ ለውጦች ሊደረጉ ይችላሉ። በዚህ ሁኔታ የልጁን IEP ለማሻሻል ወይም ለማስተካከል ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል። በወላጆች ጥያቄ፣ የትምህርት ቤቱ ዲስትሪክት ማሻሻያዎችን ያካተተ የተሻሻለውን የ IEP ቅጂ ለወላጅ መስጠት አለበት። የ IEP ወይም የልጅዎ የልዩ ትምህርት አገልግሎቶች ተቀይረዋል ብለው ካሰቡ፣ በስምምነት የተደረጉ ማሻሻያዎችን ጨምሮ የቅርብ ጊዜውን IEP ቅጂ ዲስትሪክቱን ይጠይቁ። በ IDEA ስር፣ የትምህርት ቤት ዲስትሪክቶች የ IEP ስብሰባዎችን እንዲቀንሱ ይበረታታሉ።

ያለ ፍቃዴ በልጄ IEP ላይ ለውጦች ቢደረጉስ?

ስለሚያሰጋዎት ነገር ወድያውኑ ከትምህርት ቤቱ ጋር ይነጋገሩ። የ IEP ቡድኑ አባል ኖት እና ስለ ልጅዎ ልዩ የትምህርት ፕሮግራም ሁሉም የእርስዎ ውሳኔ መካተት አለበት። ከትምህርት ቤቱ ሰራተኞች ጋር መደበኛ ባልሆነ መንገድ በመነጋገር አለመስማማቶችን መፍታት የማይችሉ ከሆነ፣ ለበለጠ አማራጮች ስለክርክር አፈታት እትም ክፍል VII ን ያንብቡ።

ልጄ አንድ ጊዜ ለልዩ ትምህርት ብቁ ከሆነ በኋላ፣ ሌላ ተጨማሪ ግምገማ ይኖራል?

አዎ፣ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ቢያንስ በሶስት አመት አንዴ፣ እና አስፈላጊ ከሆነ በብዛት መመዘን አለባቸው። IEP በአመት አንዴ የሚገመገም ቢሆንም፣ የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች በብዛት ድጋሚ መመዘኛ መውሰድ አያስፈልጋቸውም። ተደጋጋሚ ግምገማዎች ቢያንስ በሶስት አመት አንዴ ይደረጋሉ። ወላጅ እና የትምህርት ቤቱ ዲስትሪክት የሶስት አመት ግምገማ አስፈላጊ እንዳልሆነ ሊስማሙ ይችላሉ። ሆኖም፣እነዚህ የሶስት አመት ግምገማዎች ተማሪው እንዴት እየሰራ እንደሆነ ለወላጅ እና ለትምህርት ቤቱ ዲስትሪክት አስፈላጊ መረጃ ይሰጣሉ። ተማሪው ከአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እስከ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚያጋጥመውን ለውጦች ያስቡ! ልጆዎ ድጋሚ እንዳይፈተን ከመስማማትዎ በፊት በጥንቃቄ ያስቡ ምክንያቱም ብዙ ነገሮች ባለፉት ሶስት አመታት ውስጥ ሊቀየሩ ይችላሉ። የትምህርት ቤቱ ዲስትሪክት የልጁ የትምህርት እና አገልግሎት ፍላጎቶች ለማረጋገጥ (ልጁ መሻሻል ያደረገባቸውን ሁኔታዎች አካትቶ) ወይም ወላጁ ወይም አስተማሪው ድጋሚ እንዲገመገም ከጠየቀ ተማሪውን በፍጥነት ግምገማውን ደግሞ ሊወስድ ይችላል። ነገር ግን፣ ወላጅ እና ዲስትሪክቱ ግምገማ አስፈላጊ እንደሆነ ካልተስማሙ በስተቀር ግምገማዎች በአመት ከአንድ ጊዜ በላይ በተደጋጋሚ ላይደረጉ ይችላሉ። የድጋሚ ግምገማ አላማዎች የሚከተሉትን ለመወሰን ነው፦

 1. ተማሪው የብቃት መስፈርቱን ማሟላት መቀጠሉን
 2. የ IEP ግቦችን ለመምታት ተጨማሪ የሚያስፈልጉ አገልግሎቶች ምን እንደሆኑ
 3. የተማሪው የአሁን የትምህርት ስኬት ደረጃዎች እና ተያያዥ ገንቢ ፍላጎቶች።

የ IEP ቡድኑ የተማሪውን የግምገማ መረጃ እና ከላይ የተዘረዘሩትን ሶስት ጉዳዮች ለመፍታት መመልከት እና ምን ተጨማሪ ምዘና አስፈላጊ ከሆነ፣ እንደሚያስፈልግ መወሰን አለበት።

ለአካል ጉዳተኛ ልጄ በእሱ ወይም በእሷ IEP የተገለጸውን አገልግሎቶች የት አገኛለሁ?

አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች በምንም ሁኔታ ሳይገደቡ መማር አለባቸው- እንዲሁም አጠቃላይ የትምህርት ክፍልንም ማለት ሊሆን ይችላል። የ IDEA ዋና መርህ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎችን በአጠቃላይ የትምህርት ፕሮግራም ውስጥ በተቻለ መጠን ማካተት ወይም አለማስቀረት ወይም ተለይተው እንዳይማሩ ነው። አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች በምንም ሁኔታ ሳይገደቡ የመማር መብት አላቸው። ይህ ማለት የ IEP ቡድኑ ልክ አካል ጉዳተኛ ላልሆኑ ተማሪዎች ትምህርታዊ፣ ትምህርታዊ ያልሆነ፣ እና ከመደበኛ ትምህርት ውጪ የሆኑ ተግባራትን በተመሳሳይ ቅንብሮች ውስጥ ማስተማር እንዲሁም አገልግሎቶችን ለተማሪው መስጠት አለበት። አንድ አካል ጉዳተኛ ተማሪ ከአጠቃላይ የትምህርት ክፍል ቅንብር ሊወጣ የሚችለው ፍላጎቶቹ በጣም ከባድ ከሆኑ ወይም የሚረብሹ ከሆነ ወይም እርሱ ወይም እርሷ ተጨማሪ ድጋፍ እና አገልግሎት ቢደረግለትም፣ በትምህርቱ እድገት ማሳየት ካልቻለ ብቻ ነው። በአጠቃላይ የትምህርት ክፍል ውስጥ ያለ ድጋፍ ስኬታማ የሚሆኑት ሁሉም አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች አይደሉም። አንዳንድ ተማሪዎች በክፍል ከአስተማሪዎች የግል እርዳታ፣ ወይም የስርዓተ ትምህርት ማሻሻያ፣ ቁሳቁሶች፣ ወይም የመመሪያ ዘዴዎች ያስፈልጋቸዋል። ሌሎች ተማሪዎች እንደ ልዩ የትምህርት ቀን ወይም የቤት መመሪያ ያሉ፣ ሙሉ በሙሉ የተለየ ቅንብር ያስፈልጋቸዋል። አንዳንድ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች በአጠቃላይ የትምህርት ቅንብር ውስጥ ሊሰጡ ከሚችሉት በላይ መሰጠት ስላለበት ሁሉም የትምህርት ቤት ዲስትሪክት የተለያዩ የትምህርት ቅንብሮች መኖራቸውን ማረጋገጥ አለበት። ተማሪዎች ለአጠቃላይ ትምህርት ክፍል በጣም ቅርብ የሆነውን የተቀናበረ ትምህርት መማር አለባቸው፣ ነገር ግን እኛ አሁንም ተማሪው በትምህርቱ እድገት እንዲኖረው እናደርጋለን። ይህ የትምህርት ቅንብሮች ብዛት አንዳንድ ጊዜ ቀጣይነት ያለው ምደባዎች ይባላሉ እና በግራ በኩል ባለው ቻርት ላይ የተገለጹትን አማራጮች ሊያካትቱ ይችላሉ።

ልጄ IEP ቢኖረው እና በትምህርት አመቱ ዝውውር ብናደርግ ምን ሊፈጠር ይችላል?

 1. የከተማ ውስጥ ዝውውር፦አዲሱ የትምህርት ቤት ዲስትሪክት አዲስ IEP እስከሚያወጣ ወይም የቀድሞውን በስራ ላይ እስከሚያውል ድረስ ለተማሪው ከቀድሞው ዲስትሪክት IEP ላይ ከተዘረዘሩት አገልግሎት ጋር የሚመሳሰል መስራት አለበት።
 2. ከከተማ ውጪ ዝውውር፦ በአዲሱ ከተማ ያለው አዲሱ ዲስትሪክት ለተማሪው አዲስ የ IEP መመዘኛ እስኪያዳብር ድረስ፣ በቀድሞው ዲስትሪክት IEP ከተገለጹት ጋር የሚመሳሰሉ አገልግሎቶች መስጠት፣ እና አስፈላጊ ከሆነ አዲስ IEP መስራት አለባቸው።

 

በሁለቱም ሁኔታዎች፣ አዲሱ ትምህርት ቤት የልጁን የልዩ ትምህርት መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ምክንያታዊ እርምጃዎችን መውሰድ አለበት እና የቅድሞው ትምህርት ቤት መረጃ የማግኘት ጥያቄውን ወዲያውኑ ምላሽ መስጠት አለበት።

አካል ጉዳተኛው ልጄ በበጋ የልዩ ትምህርት አገልግሎቶችን ማግኘት ይችላል?

አዎ።

 1. Extended school year (ESY፣ የተራዘመ የትምህርት ዘመን) አገልግሎቶች

የ IEP ቡድን ተማሪው ትርጉም ያለው ትምህርት እንዲያገኝ አገልግሎቶቹ አስፈላጊ መሆናቸውን ከወሰነ አካል ጉዳተኛው ተማሪ በበጋ ወቅት የልዩ ትምህርት አገልግሎቶችን ማግኘት ይችላል። ለተራዘመ የትምህርት ዘመን አገልግሎት ብቁነት በሚከተሉት ሁኔታዎች ላይ የተመሰረተ ሊሆን ይችላል።

 • ተማሪው በበጋ ወቅት ችሎታውን የማጣት እድል ካለው
 • ተማሪው የበጋ ፕሮግራም አመታዊ የ IEP ግቦችን እንዲያሳካ የሚያያስፈልግ ከሆነ
 • በባለሙያ ምክር
 • በተማሪው የትምህርት ታሪክ

ተማሪው የተራዘመ የትምህርት አመት አገልግሎት እንደሚያስፈልገው በሚወሰኑበት ጊዜ የትምህርት ዲስትሪክቶች ለ IEP ቡድኖች የሚጠቀሙባቸውን መመዘኛዎች ማዘጋጀት ይጠበቅባቸዋል። ልጅዎ የተራዘመ አመት አገልግሎት እንደሚያስፈልገው ካሰቡ፣ የዲስትሪክቱን መመዘኛ ቅጂ ይጠይቁ። የበጋ ፕሮግራሙ ከተሰጠ፣ የ IEP ግቦችን ማሟላት ይኖርበታል። በሌላ አነጋገር ለሁሉም ተማሪዎች በሚሰጡ የአጠቃላይ የበጋ ትምህርት አቅጣጫዎች ላይ መሳተፍ ብቻ በቂ ላይሆን ይችላል። የተማሪው IEP በትምህርት አመቱ አንድ-ለአንድ ረዳት ካቀረበ፣ እርሱ ወይም እርሷ የአንድ-ለአንድ ረዳት በበጋ ጊዜ እንዲሁ ሊሰጣቸው ይገባል። የተራዘመ ትምህርት ፕሮግራሙ ለተማሪው ያለምንም ክፍያ መሰጠት አለበት። ዲስትሪክቱ ለተራዘመ የትምህርት አመት አገልግሎት ብቁ ለሆነ ተማሪ የተሟላ የበጋ ፕሮግራም ከሌለው ሊያዘጋጅ ወይም ለተማሪው ከፍሎ በሌላ የትምህርት ዲስትሪክት ላይ ወይም በግል ድርጅት በሚሰጠው ፕሮግራም ላይ እንዲሳተፍ ማድረግ አለበት። ዲስትሪክቱ ለተራዘመ አመት ፕሮግራም ለመጓጓዣ እና ለሌሎች ተያያዥ ወጪዎች ክፍያ መፈጸም አለበት።

 1. የአጠቃላይ የበጋ ትምህርት እርዳታዎች እና አገልግሎቶች

አካል ጉዳተኛው ተማሪ ለ ESY አገልግሎት ብቁ ካልሆነ ነገር ግን በዲስትሪክቱ አጠቃላይ የበጋ ትምህርት ፕሮግራም ከተመዘገበ፣ ትምህርት ቤቱ እርዳታዎችን እና ልዩ መመሪያ ለተማሪው መስጠት አለበት። ልጅዎ ተጨማሪ እርዳታ ካስፈለገው በ IDEA ወይም በአንቀፅ 504 ስር ያሉትን እነዚህን አገልግሎቶች ይጠይቁ።

ልዩ የትምህርት ፕሮግራሙ ልጄን ከትምህርት ቤት ወደ የአዋቂ ህይወት ሲሽጋገር ይረዳዋል?

አዎ፣ ልዩ ትምህርት የሽግግር አገልግሎቶችን ለተማሪዎች ቢያንስ ከአስራ ስድስት አመት ጀምሮ ያቀርባል። ልዩ ትምህርት ለሁሉም አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ለአዋቂ ህይወት የሚያዘጋጃቸውን አገልግሎት ያቀርባል። እነዚህ አገልግሎቶች፣ “የሽግግር አገልግሎቶች” ተብለው የሚጠሩት፣ከትምህርት እስከ ድህረ-ትምህርት ያሉትን እንቅስቃሴዎች ለማስተዋወቅ፣ኮሌጆችን ጨምሮ እና ሌሎች የሁለተኛ ደረጃ ድህረ-ትምህረት፣ የሙያ ስልጠና ፕሮግራሞች፣ ገለልተኛ የኑሮ ፕሮግራሞች፣ ለአዋቂዎች አገልግሎት፣ እና ለስራ ድጋፍ ተነድፈዋል። የትምህርት ዲስትሪክቶች የሽግግር እቅዶች ውጤታማ እንዲሆኑ ከመጀመሪያው IEP ብዙ ሳይቆዩ ተማሪው 16 አመት ሲሞላው ለትልልቅ ተማሪዎች መጀመር አለባቸው። ይህ ማለት ተማሪዎቹ 16 አመት ከመሙላታቸው በፊት የትምህርት ዲስትሪክቱ የሽግግር እቅዱን በአመታዊ የ IEP ስብሰባ ላይ መፍትሄ መስጠት ይኖርበታል። ሽግግሩ መፍትሄ ካገኘ በኋላ፣ IEP ከስልጠና፣ ከትምህርት፣ ከስራ ስምሪት ጋር በተያያዘ ተገቢ የሆኑ፣ ሊለኩ የሚችሉ ቀጣይ ግቦችን ማካተት አለበት፣ እና እንደ አስፈላጊነቱ ተማሪው፣ ራስን የመቻል የኑሮ ክህሎት እና የሽግግር አገልግሎቶችን፣ የጥናት አቅጣጫን ጨምሮ፣ እነዚህ ግቦች ላይ መድረስ አለበት። እነዚህ ግቦች በእድሜ አግባብ ባለው የሽግግር ግምገማ ላይ የተመሰረቱ መሆን አለባቸው። ተማሪው የሚያገኛቸው እንደዚህ የሽግግር አገልግሎት አይነቶች በእርሱ ወይም በእርሷ ፍላጎት እና ምርጫ ላይ የተመሰረቱ እና ክህሎቶቻቸውን ግምት ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

የተተረጎመ የልጄን IEP ቅጂ ማግኘት እችላለሁ?

አዎ፣ የልጅዎን Individualized Educational Plan (IEP፣ ግላዊ የድደረገ ትምህርታዊ ዕቅድ) መረዳት እንዲችሉ ከፈለጉት የተተረጎመ ቅጂ ማግኘት መቻል አለብዎት።

በልዩ ትምህርት ህጎች መሠረት፣ ዲስትሪክቶች የልዩ ትምህርት ፈቃድ ቅጾችን እና prior written notices ቀዳሚ የጽሑፍ ማሳወቂያዎችን” መተርጎም አለባቸው። የልዩ ትምህርት ህጎቹ IEP ን እራሱ ስለመተርጎም የተለየ ነገር አይናገሩም። ነገር ግን፣ የ US Department of Education (የዩኤስ የትምህርት መምሪያ) እና US Department of Justice (የዩኤስ የፍትህ መምሪያ) Civil Rights Act (የሲቪል መብቶች ህግ) ርዕስ VI ን ለማክበር ዲስትሪክቶች የ IEP ዎችን ትርጉም ለመስጠት ዝግጁ መሆን እንዳለባቸው አብራርተዋል። የሚያብራሩት፦

በርዕስ VI መሰረት፣ የተማሪን IEP ጨምሮ፣ ሁሉም አስፈላጊ ሰነዶች ለ LEP [የተገደበ የእንግሊዝኛ ችሎታ ያለው] ወላጆች ተደራሽ መሆን አለባቸው፣ ነገር ግን ይህ ማለት ሁሉም አስፈላጊ ሰነዶች በዲስትሪክቱ ውስጥ ላሉ ቋንቋዎች መተርጎም አለባቸው ማለት አይደለም። ለምሳሌ፣ ወቅታዊ እና የተሟላ የቃል ትርጉም ወይም የአንድ አስፈላጊ ሰነድ የተተረጎመ ማጠቃለያ በአንዳንድ ሁኔታዎች ውስጥ በቂ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን፣ አንድ ዲስትሪክት ለ IEP ትርጉም ያለው ተደራሽነት እና ከእሱ ጋር የተያያዙ የወላጅ መብቶችን ለመስጠት ወቅታዊ እና የተሟላ የተተረጎመ IEPዎችን ለማቅረብ መዘጋጀት አለበት። ይህ የሆነበት ምክንያት ወላጅ በ IEP ስብሰባ ወቅት ብቻ ሳይሆን በሁሉም የትምህርት ዓመታት የልጁን እድገት ለመከታተል እና የ IEP አገልግሎቶች መሰጠታቸውን ለማረጋገጥ ትርጉም ያለው የ IEP ተደራሽነት ማግኘት ያስፈልገዋል።

https://sites.ed.gov/idea/files/policy_speced_guid_idea_memosdcltrs_iep-translation-06-14-2016.pdf

የልጅዎን የ IEP ቡድን የተተረጎመ ቅጂ ከፈለጉ፣ በልጅዎ ትምህርት ቤት ዲስትሪክት ውስጥ ያለውን የልዩ ትምህርት ክፍል ያነጋግሩ።  

ጥያቄዎች ወይም ስጋቶች ካሉዎት፣ እባክዎን ወደ Office of Economic Opportunity (OEO፣ ምጣኔ ሃብታዊ ዕድል ቢሮ) ይደውሉልን እና እኛ ለመርዳት መሞከር እንችላለን።