ውጤታማ በሆነ መልኩ በትርጉም መግባባት

የትርጓሜ ምክሮች ካርድ
Communicating Effectively with Interpretation

ውጤታማ በሆነ መልኩ በትርጉም መግባባት

 • Schools and districts must provide interpretation when needed to communicate effectively with families who request an interpreter.
 • አስተርጓሚ ከጠየቁ ቤተሰቦች ጋር በደንብ ለመግባባት ትምህርት ቤቶች እና ወረዳዎች/አውራጃዎች የትርጉም አገልግሎት ማቅረብ አለባቸው።
 • For interpretation to be effective, everyone involved in the conversation must cooperate and make time for interpretation.
 • ትርጓሜ ውጤታማ እንዲሆን፣ በንግግሩ/በውይይቱ ውስጥ የተሳተፈ ሁሉም ሰው መተባበር እና ለትርጉም ጊዜ መስጠት አለበት።
 • Use this card as needed during an interpreted conversation to receive a complete, accurate and understandable interpretation.
 • የተሟላ፣ ትክክለኛ እና ለመረዳት የሚቻለውን ትርጓሜ ለመቀበል በተተረጎመ ውይይት ወቅት ይህንን ካርድ እንደ አስፈላጊነቱ ይጠቀሙ።
 • Remember, if you do not understand something; ask the person you are talking with to explain. The interpreter can interpret your request for explanation but should not try to answer your questions.
 • ያስታውሱ፣ አንድ ነገር ካልገባዎት፤ የሚያነጋግሩትን ሰው እንዲያብራራልዎት ይጠይቁ። አስተርጓሚው ለማብራሪያ ያቀረቡትን ጥያቄ መተርጎም ይችላል ግን ጥያቄዎችዎን ለመመለስ መሞከር የለበትም።
 • If you believe the interpreter is not interpreting correctly, you can ask to re-schedule with another interpreter.
 • አስተርጓሚው በትክክል እያስተረጎመ እንዳልሆነ ካመኑ፣ ከሌላ አስተርጓሚ ጋር እንደገና ቀጠሮ ለመያዝ መጠየቅ ይችላሉ።
 • Pardon me, I would like to ask…
 • ይቅርታ ያድርጉልኝ፣ የሚከተለውን መጠየቅ እፈልጋለሁ...
 • Please pause so the interpreter can tell me what you have said.
 • አስተርጓሚው ያሉትን እንዲነግረኝ እባክዎን ያቁሙ።
 • Please repeat that, I am afraid it was not all covered in the interpretation.
 • የተናገሩት በሙሉ በትርጉሙ ውስጥ እንዳልተካተተ እሰጋለሁ፣ እባክዎን ይድገሙት።
 • Could we slow down a bit to be sure the interpreter is able to give a full interpretation?
 • አስተርጓሚው ሙሉ ትርጓሜ መስጠት መቻሉን ለማረጋገጥ ትንሽ ቀስ ማለት እንችል ይሆን?
 • Could you both repeat what you said, one at a time, so we can be sure the interpreter can cover everything?
 • አስተርጓሚው ሁሉንም ነገር መተርጎም እንደሚችል እርግጠኛ ለመሆን ሁለታችሁም የተናገራችሁትን አንድ በአንድ መድገም ትችላላችሁ?
 • I do not understand the interpretation very well. Could we try to reschedule with another interpreter?
 • ትርጓሜው በደምብ አልገባኝም። ከሌላ ተርጓሚ ጋር በሌላ ጊዜ ቀጠሮ ለመያዝ መሞከር እንችላለን?

Interpretation Support Tips Card Printable PDF

የትርጓሜ ምክሮች ካርድ